Thursday, April 18, 2019

ጠ/ሚ አብይ አህመድ ኢትዮጵያን በለውጥ ሃዲድ ያስቀጥሉ ይሆን? Chatham House article

Abel Abate and Ahmed Soliman

ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ስልጣን መምጣት ወዲህ ኢትዮጵያ በፈጣን የለውጥ ጎዳና ላይ ትገኛለች፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መጠነ ሰፊ የማሻሻያ እርምጃዎችን በመውሰድ አምባገነን የነበረውን የመንግስት መዋቅር ከመቀየር አንስቶ ኢትዮጵያ በአካባቢው ከሚገኙ አገራት ጋር የነበራትን ግንኙነት በማሻሻላቸው ከፍተኛ አለም አቀፍ እውቅና ተችሯቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ለዚህ አመት የኖቤል የሰላም ሽልማት ሁሉ ለመታጨት በቅተዋል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ከፍተኛ ሊባል የሚችል ህገ ወጥነት፣ በክልሎች ውስጥና በክልሎች መካከል የቀጠለ ግጭት፣ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችና ከፍተኛ የሃገር ውስጥ መፈናቀል ተከስቷል፡፡

በዚህም ምክንያት በመጀመሪያዎቹ የስልጣን ወራት ለጠ/ሚሩ የተቸረው እጅግ ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ባጋጠሙ ቀውሶች ምክንያት በቅርብ ጊዜያት ውስጥ መቀዛቀዝ ተስተውሎበታል፡፡ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ፣ በአንዳንድ ተጻራሪ አመለካከት ባላቸው አካላት ጭምር፣ ከፍተኛ የለውጥ ፍላጎትን የቀሰቀሰው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የስልጣን ጉዞ ከታሰበው በተቃራኒ መልካም አስተዳደርም ሆነ ሰላምን ሳያመጣ እንዳይከሽፍ ብዙዎች ይሰጋሉ፡፡ ቢያንስ ግን እስካሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ስኬቶች ከችግሮቻቸው ልቀው ይታያሉ፣ ከባድ ፈተናዎቸ ከፊት ለፊት መኖራቸውን ሳይካድ፡፡


Read more on Chatham House website

No comments:

Post a Comment